አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ ማራዘሚያ!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ከተማ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የጸዱ ቦታዎችን ጨምሮ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በኮልፌ ቀራንዮ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በየካ፣ በቦሌ፣ በአዲስ ከተማ፣ በቂርቆስ፣ በጉለሌ፣ እና በልደታ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
የጨረታውን ሰነድ ከሚያዚያ 24/2016 ዓ.ም እስከ ግንቦት 9 /2016 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ
2. ማንኛውም በዚህ የመሬት ሊዝ ጨረታ ለመሳተፍ የፈለገ ተጫራች በተራ ቁጥር 1 ላይ በተገለጸዉ ዌብ ሳይት የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በመጀመሪያ በስሙ (ወይም በሕጋዊ ተወካይ) የቴሌ ብር አካውንት በመክፈት ከአካውንቱ ተቀናሽ በማድረግ ሰነዱን መግዛት ይጠበቅበታል።
3. ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ቦታ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎችን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ አለባችሁ።
4. አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት አይችልም። በመሆኑም ከአንድ በላይ ቦታ ተጫርቶ ከተገኘ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መስፈርት መሠረት መሆን ይኖርበታል።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘውን ጠቅላላ ዋጋ 50% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ለየቦታ ኮዱ በጋዜጣው ላይ የተቀመጠውን መጠን ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ 50% ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል። እንዲሁም አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም። ከአዲስ አበባ ውጪ ከሚገኙ ባንኮች ሲፒኦ ስታሠሩ አዲስ አበባ ከሚገኙ ባንኮች በኔትወርክ የተያያዘ መሆን አለበት፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ችግር ቢፈጠር ጽ/ቤቱ አይጠየቅም።
7. ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ስትመልሱ፣
ግንቦት 9/2016 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አካባቢ ኤም ኤ (M A) ሕንጻ ላይ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 12/2016 ዓ.ም ከቀኑ 3:00 ሰዓት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ የሚከፈት ሆኖ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል። ተጫራቾች ቦታውን በአካል ለመመልክት ከፈለጉ በ14/8/16ዓ.ም፣16/08/16 ዓ.ም እና በ18/08/16 ዓ.ም ጠዋቱ በ3፡00 እና ከሰዓት በ8፡00 ሰዓት ለጨረታ የተዘጋጁ ቦታዎች የሚገኙበት ክ/ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ለዚህ ሥራ በሚመደቡ አስጎብኝዎች አማካኝነት ቦታዎቹን መመልከት ይቻላል።
9. ጨረታውን ያላሸነፉ (ተሸናፊ) ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ሲፒኦ የጨረታው አሸናፊዎች በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከተገለጸበት ከ15 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አጫራቹ መ/ቤት ለባንክ በመላክ | ወዳሠሩበት የባንክ ሂሳብ ተመላሽ ይደረጋል። በካሽ ያሠሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን ለመረከብ በቅድሚያ የሲፒኦውን ጉርድ ኮፒ ማቅረብና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቀርበው መውሰድ አለባቸው። ከላይ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ካልወሰዱ ለሚፈጠረው ችግር አጫራቹ መ/ቤት ተጠያቂ አይሆንም።
10. መሥሪያ ቤቱ (ቢሮው) የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፡-
በስልክ ቁጥር +251 11 156 6440 መረጃ ማግኘት ይቻላል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ