የኦቪድ ቤቶች ባንክ አክሲዮን ማህበር


Mobile +251 904 151 411
Mobile 2 +251 942 514 203
Mobile 3 +251 912 422 723
LocationBole Sub-City, W-03, Office # 386, Platinum Bldg. 4th Floor (near Desalegn Hotel), Addis Ababa, Ethiopia
Primary CategoryBanking
የኦቪድ ቤቶች ባንክ አክሲዮን ማህበር

I. መግቢያ

ባንኩ የሚመሰረተው በኢትዮጲያ ንግድ ህግ አንቀጽ 245፣ በባንክ ስራ አዋጅ ቁጥር 592/2000 እና የባንክ ስራ አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 1159/2011 መሰረት ባለአክሲዮኖች እየፈረሙ በሚገዙት አክስዮን ነው፡፡

የኦቪድ ቤቶች ባንክ አደራጆች የሚመሰረተው ባንክ የተሻለ ትርፍ የሚያስገኝ  እና ዘላቂ እንደሚሆን ያምናሉ፣

ባንኩም ከትርፍ ባሻገር በአገራችን የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ፣ አካታችና ለኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን አስተዋፆ ያበረክታል።

1. የኦቪድ ቤቶች ባንክ አክሲዮን ማህበር መቋቋም አስፈላጊነት

      • የዓለም ባንክ በተለያየ ጊዜ ባወጣዉ ሪፖርት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዓለም ፈጣን ዕድገት እያስመዘገቡ ካሉት አገሮች መካከል አንዱ መሆኑን ይገልፃል፡፡
      • በመንግስትና በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ላይ የተደረጉ አዎንታዊ እርምጃዎች ማለትም የኮንስትራክሽንና ግንባታ ስራ መስፋፋት፣ የአምራች ኢንዱስትሪ ፓርኮች በመገንባት ሥራ መጀመርና፣ የዉጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች ለተመዘገበው የኢኮኖሚ ዕድገት ተጠቃሽ ምክንያቶች መሆናቸዉን እንረዳለን።
      • በዚህ የኢኮኖሚ ዕድገት የባንክ ኢንዱስትሪዉ ሚና በተለይ ደግሞ ለዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር፣ ለኢንቨስትመንት የሚሆን ገንዘብ በማቅረብ፣ የዜጎች የቁጠባ ባህል በማሳደግ፣ ባንክ ስራ ላይ መዋለ-ንዋይ ለሚያፈሱ ባለሀብቶች ተመጣጣኝ ትርፍ መስጠት፣ የዉጭ ንግድ ማበረታታትና፣ በግብር ከፋይነት እጅግ ከፍተኛ ሆኖ እናገኘዋለን።
      • በሌላ በኩል አገራችን በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ሁለተኛ ብትሆንም የቤቶች ፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽነትና አካታችነት እንዲሁም ለኢንቨስትመንት የሚሆን የገንዘብ ሀብት በማሰባሰብና በማቅረብ ረገድ ገና ብዙ መስራት እንዳለበት የተለያዩ ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡
      • የኢትዮጵያ መንግስትና የዓለም ባንክ እ.ኤ.አ. 2015 በጋራ ባደረጉት ጥናት መሰረት የከተሞች መስፋፋትና ዕድገት እጅግ እየጨመረ በመምጣቱ የመኖሪያ ቤቶችን የቤት ፍላጎት ማሟላት አለመቻሉን ተገልፇል።
      • ችግሩንም ለመቅረፍ የቤቶች ፋይናንስ ስርዓት በመገንባት ለልማትና ግንባታ የሚውል ብድር አቅርቦት የሚጭምርበትን ሁኔታ ማመቻቸት የመንግስት ተቀዳሚ ዓላማ መሆኑ ተገልፇል።
      • በዚህ ጥናት መሰረት የኢትዮጵያ የከተሞች ዕድገት ግምገማ ትንበያ እ.ኤ.አ. ከ2017 እስከ 2037 ባለው ጊዜ ውስጥ የዜጎች የቤት ፍላጎት ለማሟላት ቢያንስ በየዓመቱ 381,000 ቤቶች እየተገነቡ ለገበያ መቅረብ ይኖርባቸዋል።
      • በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ መገንባት ይችላሉ ተብሎ ታሳቢ የተደረገው በዓመት ከ165,000 ያነሱ ቤቶች ናቸው።
      • ከዚህ መረዳት የምንችለው በኢትዮጵያ የመኖሪያ የቤቶች አቅርቦትና ፍላጎት እጅጉን የተራራቀ መሆኑን ነው።
      • ምንም እንኳን የኮንስትራክሽን እና ሪል እስቴት ዘርፍ ለአገር ኢኮኖሚ ከ20% በላይ አስተዋጸዖ ቢኖረዉም እንዲሁም ለዜጎች ማህበራዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጾ ያለው ዘርፍ ቢሆንም ለዘርፉ የተሰጠው ብድር ከ10% በታች ነው፡፡
      • ስለሆነም የኮንስትራክሽን ክፍለ ኢኮኖሚው በተለይ የመኖሪያ ቤቶች እና እንዱስትሪዎች ግንባታ ላይ የባንኮች ትኩረት የሚፈለገውን ያህል እንዳልሆነ አደራጆች ተገንዝበዋል።
      • በሌላ በኩል የመንግስት አቅጣጫ የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ ዘርፉን በማዘመን የኢኮኖሚ መዋቅር ለዉጥ እንዲያቀላጥፍ ይጠበቃል።
      • ይህ የመንግስት ፍላጎት ያለ በቂ የባንክ አገልግሎት ማሳካት እየተቻለ አይደለም፣ ክፍተቱን ለመሙላት የመንግስት ጥረትና አሁን ላይ ያሉ ባንኮች በቂ ስላልሆኑ ተጨማሪ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት እንደሚያስፈልጉ ታምኗል።
      • ስለዚህ አደራጅ ኮሚቴዉ ይህንን ዕውነታ ተገንዝቦና፤ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታና ግዢ ብድር እንዲሁም ሌሎች የባንክ አገልግሎቶችን በመስጠት የበኩሉን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አበርክቶ በማድረግ ለባለአክሲዮኖች ዘላቂና ጠቀም ያለ ትርፍ ለማስገኘት በማሰብ የኦቪድ ቤቶች ባንክ አክሲዮን ማህበርን ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።

II. ዓላማ

      • ባንኩ የፋይናንስ አገልግሎት አካታችና፣ ተደራሽ በማድረግ የገንዘብ ሀብት ከማህበረሰቡ በማሰባሰብ
      • ለቤቶች ግዥ፣ ግንባታ፣ ዕድሳትና ማሻሻያ ብድር በማቅረብ የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ዕጥረት በመቅርፍ ረገድ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ፣
      • ሌሎች የባንክ አገልግሎቶችን በመስጠት የፋይናንስ አካታችነትን ማገዝ፤
      • ለባለ አክሲዮኖችም ጠቀም ያለ እና አስተማማኝ ትርፍ ማስገኘት ነው፡፡

III. ተግባር

      • ተቀማጭ ገንዘብ ከግለሰቦች፣ ከግል ድርጅቶች፣ ከመንግስትና፣መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ማሰባሰብ፣
      • ለቤት መግዣ፡ መስሪያና ማደሻ ብድር መስጠት፤
      • ለተለያዩ የኢኮኖሚ ክፍሎች አዋጭነት መሰረት በማድረግ የረጅም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ብድር ማቅረብ፣
      • ዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት መስጠት፣ የቃልኪዳን ሰነዶች መስጠት፤
      • ከወለድ ነፃ የሆኑ የባንክ አገልግሎት፣ ­የደንበኛ ወኪል በመሆን በአደራ ገንዘብ ማስተዳደርና አክሲዮን መሸጥና ገንዘብ ማስተላለፍ፣
      • ­የውጭ ምንዛሪ መግዛትና መሸጥ፣ ­በካፒታል ገበያ ላይ መሳተፍ፣ ­ሌሎች ከላይ በዝርዝሩ ያልተካተቱ የባንክ አገልግሎችን መስጠት

V. የአክሲዮን ብዛት፣ ዋጋና ሽያጭ

      • የባንኩ አክስዮኖች እኩል ዋጋ ያላቸው አንድ ዓይነትና ተራ አክስዮኖች ናቸው፡፡
      • ለሽያጭ የቀረቡ አክስዮኖች ብዛት 20,000,000 (ሃያ ሚሊዮን) ሲሆን የአንድ አክስዮን ዋጋ ብር 1,000 (ብር አንድ ሺ) ነው፡፡
      • አንድ ባለአክስዮን ሊገዛ የሚገባው ዝቅተኛው የአክሲዮን ብዛት200 ወይም ብር 200ሺ ሲሆን ከፍተኛ የአክስዮን መጠን ደግሞ 1 ሚሊዮን አክስዮን ወይም ብር 1 ቢሊዮን የሚያወጣ አክስዮኖች ነው፡፡
      • ባላክስዮኖች ከፈረሙት አክስዮን ዉስጥ ቢያንስ 25% አክስዮኖቹ ሲፈረሙ መክፈል አለበት፡፡ ቀሪውን በአንድ ጊዜ ወይም በተለያየ ጊዜ ከምስረታው ጉባኤ በኋላ ባሉት ተከታታይ ሁለት ዓመታት ውስጥ መከፈል ይኖርበታል፡፡
      • አክስዮን ገዥዎች ለመግዛት በፈረሙባቸው አክስዮኖች ላይ 5% የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ፤
      • ባንኩ አክስዮን የሚሸጠው በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ፈቃድ በተለያዩ ባንኮች በኩል በተከፈቱ ዝግ ሂሳቦች አማካኝነት ነው፣
      • የአክስዮን ግዢ ቅጾች ከባንኩ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ወይም ከድህረ ገጽ በማውረድ መሙላት ያስፈልጋል፣

VIII. ማጠቃለያና አስተያየት

      • የቤቶች ባንክ መቋቋም አስፈላጊነትን የሚያጎሉ ምክንያቶች፣
      • የአገራችን የቤት ልማት ዘርፍ ክፍተኛ የሆነ የአቅርቦት ችግር ያለበት መሆኑ፣
      • የአቅርቦት ችግሩ ከፍተና የሆነ የማህበራዊ ቀዉስ እየፈጠረ መሆኑ፣
      • መንግስት ይህን ችግር ለመቅረፍ የመንግስና የግል አጋርነት የሚል ፖሊሲ አውጥቶ ዘርፉን እየደገፈ መሆኑ፣
      • በዚህ ሂደት የባንኮች ሚና ከፍተኛ ቢሆንም አሁን ያሉት ባንኮች ለዘርፉ የሰጡት ትኩረት አናሳ መሆኑ ይገኙበታል

ኦቪድ ቤቶች ባንክ ሲመሰረት

      • በከፍተኛ ካፒታል ይመሰረታል፤
      • የአግር ዉስጥና የዉጭ አገር ባለሃብቶችን አሳታፊ ባንክ ይመሰረታል፣
      • ለቤት ልማት ከፍተኛ የሆነ ብድር ያቀርባል፣
      • ለባለአክስዮኖች በአጭር ጊዜ የተሻለ እና አስተማማኝ ትርፍ ያስገኛል፣
      • ስለዚህ እዚህ ባንክ ላይ አክስዮን በመግዛት የአገራችንን የቤት ልማት በመደገፍ ክፍተና እና አስተማማኝ ትርፍ ተጋሪ ይሁን

Address:- Bole Atlas, Platinium Plaza 4rth floor
Mobile no:- +251 904 151 411, +251 942 514 203, +251 912 422 723, +251 942 655 060, +251 910 396 936
Website:- www.ovidbetochbank.com 


Shared Banner Directory p8