አንድነት የጥበቃና የፅዳት አገልግሎት ኃ/የተ/የግል ማህበር


Phone +251 11 533 6060
Mobile +251 991 331 282
Locationkirkos sub city kirkos cherch buliding 3 floor house no:27, Addis Ababa, Ethiopia
Primary CategorySecurity/Guard Services
አንድነት የጥበቃና የፅዳት አገልግሎት ኃ/የተ/የግል ማህበር

ድርጅታችን አንድነት የጥበቃና የፅዳት የሰው ሀይል አገልግሎት የመሰረትን በውትድርና ሙያ ለረጅም አመታት በከፍተኛ ሀላፊነት ሀገራችንን ያገለገልን ስንሆን በክብርና በጡረታ ከሰራዊቱ በመሰናበታችን ሀገርና ህዝብ በመጠበቅ በተግባር የተፈተነው ታማኝነት ልምድና ችሎታችንን ተጠቅመን የድርጅትዎን ሀብት ንብረት እና ደህንነትዎን ከመንግስት ፀጥታ ሃይል በቅርበት በመቀናጀት በአስተማማኝ ለመጠበቅ ሙሉ ሃላፊነት በመውሰድ የረጅም አመታት የጥበቃ ልምድ ባላቸው አመራር ፣ ተቆጣጣሪዎች እና የጥበቃ አባላት በመቀናጀት የስራ እድል ለፈጠሩልን ደንበኞች ባለሃብቶች የመንግስትና የግል ድርጅቶች በእርግጠኝነት ከአብዛኛው መሰል የጥበቃ ድርጅቶች በተሻለ በጥራትና በብቃት ቀን ከለሊት ሳንሰለች ልናገለግልዎ የተዘጋጀን ተመራጭ ድርጅት ነን፡፡

ድርጅታችን የተቋቋመበት አላማ

በውትድርናችን የልዩ ሙያ ባለቤት ስንሆን ካለን የስራ ልምድ እና ሙያ አንፃር በዘርፉ ብንሰማራ እኛ ተጠቅመን እኛን መሰል ሙያተኞችና ሌሎች በማሰልጠን ፍትሃዊ የሆነ ክፍያ በመክፈል የመንግስትን ህጋዊ አሰራሮች ሳይሸራረፍ በማክበር ከደንበኞች በሃላፊነት እና በተጠያቂነት የተረከብነውን ሀብት ንብረት ለመጠበቅ እኛ የድርጅቱ ባለቤት እና አመራሮች በተወካይ/በመልክተኛ/ በስልክ የምንመራ ሳይሆን ወደ ስራው በመውረድ በአካል በቅርበት እያረጋገጥን ከባለሃብቱ ፣ ሃላፊዎች ፣ ተቆጣጣሪዎች ፣ ከጥበቃ ሰራተኞቻችን በመነጋገር በመወያየት የተፈጠረ ሁኔታ (አለመግባባት መስተካከል ያለበት ወዘተ) ፈጥነን የመፍትሄ እርምጃ በመውሰድ ደንበኞች ጥበቃ በተመለከተ ያለስጋት ለእኛ አስረክበው በእኛ ተማምነው ዋና ስራቸውን ተረጋግተው እንዲሰሩ በተግባር እያሳየን ከልብ የማገልገል አላማ ሰንቀናል፡፡

የድርጅታችን ስያሜ ትርጉም

ሀ. የድርጅታችን ስያሜ አንድነት የጥበቃና የፅዳት አገልግሎት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚል ህጋዊ ስያሜ ያገኘ ሲሆን ህጋዊ ሰነዱ በኮፒ ተያይዟል፡፡

ለ. የድርጅታችን አርማ በግራና በቀኝ ስምንት መስመሮችና በክብ ቅርፅ ውስጥ የተቀመጠ ጋሻና ጦር ነው፡፡ ይህም ቀደምት አባቶቻችን ጦርና ጋሻ ይዘው በአንድነት በሁሉም አቅጣጫ አገራችንን ጠብቀዋል፡፡

እኛም በዚህ የስራ ዘርፍ አገልግሎታችንን ለሚጠይቁ ደምበኞች የድርጅቱ አመራር እና መላው ሰራተኞቻችን አንድነታችንን አጠናክረን ተቀናጅተን ተናበን ስንሰራ የሚያጋጥሙ ችግሮች ፈጥነን በማስወገድ ታማኝነትንና ሀቅን ይዘን አለኝታና አጥር ሆነን ከልብ እናገለግላለን የሚለውን እምነታችንን "አንድነት" የሚለውን የድርጅታችንን መጠሪያ ያንፀባርቅልናል ብለን እናምናለን፡፡

የድርጅታችን ተልዕኮ ፡- የስራ ዕድል ለፈጠሩልን የተከበሩ ደንበኞቻችን ሃብት ንብረቶቻቸውን እንደ ተቀጣሪ ሳይሆን እንደ ባለቤት ሆነን ለመጠበቅ መንግስት በሚያቀርበው የፀጥታና ደህንነት አገልግሎት ውስጥ ያለውን ክፍትት የመሙላትና የማገዝ ስራ ውስጥ በመሳተፍና እኛ ተጠቅመን በርካቶች በተፈጠረው እድል እንዲጠቀሙ ፍትሀዊ ክፍያና ብቃት ባለው አገልግሎታችን ተወዳዳሪና ውጤታማ ለመሆን ድርጅታችን የሚከተሉትን ተልዕኮዎች ይወጣል፡፡

      • የደንበኞቻችን የሚመለከታቸው የባለሀብት ወይም የድርጅቱ የጥበቃና ደህንነት የበላይ ሀላፊዎች፣ተቆጣጣሪዎች፣ስራ አስኪያጆች፣ተገልጋዮች፣ወዘተ የሚሰጠን የእርምት ጥቆማ ወይም አስተያየት በቀናነት በማየት ለትንሽም ስህተት ዋጋ በመስጠት ፈጥነን የእርምት እርምጃ እንወስዳለን፡፡ ከባለሀብቱ ከሚመለከታቸው የሥራ ሀላፊዎች እኛ የድርጅቱ አመራሮች በስራችን ላይ እንከን(አደጋ) ደርሶ እስከምናጠራ ሳንጠብቅ ምን ችግር አለ በማለት ከስራ ሀላፊዎች በአካል እየተወያየን በቅርበት እንሰራለን፡፡
      • የደንበኞቻችን የሚጠበቅ ተቋም በሀላፊነት ስንረከብ ከመረከባችን በፊት የሚጠበቀው አካባቢ የውስጥ የውጭ አጠቃላይ ይዞታ በሙያተኛ በመቃኘት ያለችግር ለመጠበቅ ማድረግ ያለብን ጥናት በዝርዝር የሚዘጋጅ ሲሆን
      • ድርጅቱን ለአደጋ የሚያጋልጡ ለእሳት አደጋ ፣ ለስርቆት የተመቻቹ የሚመስል ንብረት ፣ ለጥበቃ አመች ያልሆነ እንዲጠፋ ፣ እንዲበላሽ ፣ እንዲባክን ያለነገር ከታዘብን አስቸኳይ እንዲስተካከሉ ለሚመለከተው በፅሁፍ በወቅቱ እንዲያውቁ ይደረጋል፡፡ በስራ መሃል ከተከሰተም እናሳውቃለን፡፡
      • በእኛ ደረጃ የስራ እድል የፈጠረልን ባለሃብት ተቋም በተገልጋዮች በሰራተኞች ወይም በእኛ ሱፐርቫይዘር የአሰራር ክፍተት ቅሬታ የሰማነው የታዘብነው በስራ አጋጣሚ ከአወቅን ለሚመለከተው እንጠቁማለን እናሳውቃለን፡፡
      • የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች አጋርና ተባባሪ ሆነን ደምበኞቻችን ለፍተውና ደክመው ያገኙት ሀብት ንብረት ባለበት ሁኔታ በመጠበቅ ሰላምና መረጋጋት አግኝተው የዕለት ተዕለት ተግባሮቻቸውን ያለምንም ስጋትና እንቅፋት እንዲፈፅሙ የበኩላችንን ድርሻ መወጣት የሚያስችል የተቀናጀ እና የተዋሀደ ዘመናዊ የግል ጥበቃና ደህንነት (ፕሮቴክሽን) አገልግሎት በጥራትና በአስተማማኝ ሁኔታ መስጠት፡፡
      • በዚህ የግል ጥበቃ አገልግሎት ሴክተር ህጋዊና ፍትሀዊ ተወዳዳሪነት እንዲኖር የበኩላችንን ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ፡፡
      • መንግስት በዚህ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያወጣውንና በቀጣይ የሚያወጣቸውን አዋጆች፣ ደምቦችና መመሪያዎች መሠረት ያደረገ ግልፅነት፣ ተጠያቂነትና ሀላፊነት የሰፈነበት አሠራር መስረትና የሰራተኛውን ታማኝነት የስራ ፍላጎት የሚያሳድግ ፍትሀዊና ተገቢ ክፍያ በመክፈል የስራ ዋስትና ማረጋገጥ፡፡
      • የመንግስት የንግድ ህግና መመርያን በመተግበር በወቅቱ ገቢ በመሰብሰብ ገቢ ማድረግ፡፡
      • በዚህ የግል ጥበቃ ዘርፍ ሌሎች የበለፀጉ አገሮች የደረሱበት ደረጃ ለመድረስ የሚያስችሉ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ እውቀታችንና ችሎታችንን በማስፋት አዳዲስ አስተሳሰቦችና አሰራሮች በማመንጨት በዘርፉ የተሸለ ስራ መስራት፡፡

የድርጅታችን ራዕይ

      • በአግራችን ኢትዮጵያ በርካታ የጥበቃ ኤጀንሲ አለ፡፡ በመሆኑም ድርጅታችን አንድነት አቅም በፈቀደ ሁሉ የሰራተኞቻችንን መብት በማክበር ፍትሃዊ ክፍያ እና ግልፅ አሰራር በመከተል አክብረውና አምነው ስራ ለሰጡን ደንበኞቻችን የተሻለ አገልግሎት በመስጠት የተሻለ ኤጄንሲ እና ሞዴል በመሆን በሀገር ደረጃ ተሸላሚ፣ተመራጭ እና አስተማማኝ ብቃት ያለው ኤጄንሲ መሆን ነው፡፡

የድርጅታችን ተግባሮች ፣ የአሰራር መርሆችና እሴቶች

የድርጅታችን ተግባሮች

      • ድርጅታችን በሚሰጠው የጥበቃ አገልግሎት በአሀገራችን ያለውን የአሰሪ እና ሰራተኛ ህጋዊ አሰራር በማክበር እና ታሳቢ ያደረጉ መመሪያዎችን ያሰራር እስታንዳርዶች (የስነ ምግባር እና የአሰራር ደንብ የቅጥር የዝውውር እና የእድገት መመሪያ የጥንቃቄ ደንቦች) ወዘተ ማዘጋጀት፡፡
      • በፌደራል ፖሊስ ደንብ ፣ በድርጅቱ አሰራርና በደምበኞች ፍላጎት ጥበቃ መሆን የሚችሉ ሠራተኞችን በመመልመል የሚሠጣቸው የጥበቃ ቦታ ባህሪና ከባቢያዊ ሁኔታን ያገናዘበ ኦረንቴሽንና ስልጠና በመስጠት ማዘጋጀትና ጥበቃለማከናወን የሚያስችል የተሟላ አቅም መፍጠር፡፡
      • አሁን ያለንን እውቀትና ችሎታ ወደ ላቀ ደረጃ በማሳደግ የአገራችን የኢኮኖሚ እድገት የሚጠይቀውን አገር አቀፍ ስታንዳርድ ያሟላ የጥበቃ ፣ የእጀባ ፣ የፅዳት እና የማሰልጠን አገልግሎት ከሚመለከታቸው የመንግስት የሙያና የፀጥታ ሀይሎች ወቅታዊ ስልጠናዎችን በመውሰድና ተናብቦ በመስራት በሀገራችን ካሉት በርካታ ኤጄንሲ ብቁ እና ተመራጭ ከምርጦችም ምርጥ ሆኖ ለመገኘት ሳንሰለች እንሰራለን፡፡
      • የመንግስት ህግናደንብ ሲፈቅድ የደምበኞቻችንን ዘላቂ ፍላጎት በአስተማማኝ ሙያተኛ ለማሟላትና ለሌሎች የጥበቃ ተቋማት የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎት ምንጭ ለመሆን ደረጃውን የጠበቀ ማሰልጠኛ ማቋቋም፡፡
      • የግል የጥበቃ አገልግሎት ዘርፍ የኢኮኖሚ እድገት የፈጠረው ያለ አዋጅና ህግ በስፋት ስራላይ የዋለ ቢሆንም እንደ ሌሎቹ አገሮች በአዋጅ ላይ የተመሰረተ የራሱ መመሪያና ደንብ ያለው በህግ አግባብ የሚመራ ሴክተር እንዲሆን ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት መረጃና የሌሎች አገሮችን ተሞክሮ በማቅረብ ማገዝ፡፡
      • በጥበቃ አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ መሰል ተቋማት ውስጥ አሰራርና ገዢ አስተሳሰብ እንዲኖራቸው የሚያስችል ጠንካራ ማህበር እንዲኖራቸው የበኩላችንን ድርሻ መስራት፡፡
      • ለሰራተኞቻችን ያልተቋረጠ ስልጠና በሚሰሩበት ቦታ እና በዋናው ቢሮ ፕሮግራም አዘጋጅተን የማንቃትና በቁ የማድረግ ስራ ይሰራል፡፡
      • ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ፣ ከአቅራቢያው ፖሊስ ስልጠና ለሰራተኞቻችን እዲሰጥ እናደርጋለን፡፡
      • ልተቋረጠ የግንኙነት ስርአት ከደንበኞቻችን፣ከተቆጣጣሪዎች በአቅራቢያው ካለ ፖሊስ በስልክ እና አሰፈላጊ ሲሆን በፅሁፍ ይደረጋል፡፡
      • ልተቋረጠ የቁጥጥር ስርአት በግልፅ እና በስውር ይካሄዳል፡፡

የድርጅታችን የአሰራር መርሆዎች

      • ከዚህ በላይ የተቀመጡትን ተግባሮች ለማሳካትና ተግባራዊ ለማድረግ ከዚህ በታች የሚዘረዘሩትን የድርጅታችን የአሰራር መርሆች እንከተላለን፡-
      • ድርጅታችን የጥበቃ አገልግሎት በሚሠጥባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የፍትህና የፀጥታ አካላትጋር ግንኙነት በመመስረት ምንጊዜም አጋዥና ተባባሪ መሆን ፣ በተሰማራንባቸው የጥበቃ ቦታዎችና አካባቢዎች የታሰቡ የገጠሙና የታዩ የወንጀል ድርጊቶች ለአካባቢው የመንግስት ፀጥታ ሀይል በተቻለ ፍጥነት ማሳወቅ፡፡
      • የደምበኞቻችንንፍላጎት፣የድርጅታቸውን ውስጣዊ ባህሪና ከባቢያዊ ተፅዕኖ ያገናዘበ ደረጃውን የጠበቀ ንቁና ታማኝነት ያለው የጥበቃ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ዕቅድ ማውጣትና ከደንበኞች ጋር በመምከርና በመተማመን ስራ ላይ ማዋል ወይም መተግበር፡፡
      • ድርጅታችን የጥበቃ አባላትን የሚመለምለው በዋነኝነት አዋጅ ቁጥር 377/1996 ዓ/ም ስለ አሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ የወጣ አዋጅ የሚከተል ሲሆን ከድርጅቱ ባህሪ አንፃር በተጨማሪ ትክከለኛና ወቅታዊ አድራሻ ያላቸው መሆኑን በማረጋገጥ ፣ ለስራቸው ተመጣጣኝ ዋስትና (ተያዥ) የሚያቀርቡ፣ ከሚኖሩበት ቀበሌ ድጋፍ ያላቸውና በፌደራል ፖሊስ የጥበቃ አባላትን ስለመቅጠር የወጣውን መስፈርት የሚያሟሉትን ብቻ ይሆናል፡፡
      • ለምንቀጥራቸው የጥበቃ አባላት ለሚሠጣቸው ስራ ፣ ኃላፊነት እና የተጠያቂነት ጫና ግምት ውስጥ የሚያስገባ፣ ተረጋግተው እንዲሠሩ የስራ ዋስትና የሚሠጥና ድርጅቱ የኛ ነው የሚል የባለቤትነት መንፈስ የሚፈጥርና ታማኝነታቸውን የሚያሳድግ አሳማኝና ፍትሀዊ የደመወዝ አከፋፈል ስርዓት መከተል፡፡ (ከደምበኞች ጋር ከተደረገው የክፍያ ውል መሠረት ከ80% የማያንስ የደመወዝ ክፍያ መፈፀም)
      • በግል ጥበቃ አገልግሎት ዘርፍ ህጋዊና ፍትሀዊ ተወዳዳሪነት እንዲኖር የመንግስት አዋጆችና ደምቦች ተግባራዊ በማድረግ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው አሠራር መከተል፡፡
      • የምንሠጠው የጥበቃ አገልግሎት የሀገራችን ህገ፣ ሌሎች ከግል ጥበቃ ጋር ተያያዥ የሆኑ አዋጆችና አሰራሮች መሰረት አድርገን አገልግሎታችንን ከጠየቁ ደምበኞች ጋር በገባነው የጋራ ውል ስምምነት ብቻ ተግባራዊ ማድረግ፡፡
      • የጥበቃ አባላት የቅጥር ውል የሚፈፅሙት በተ.ቁ 8 ስር የተጠቀሰውን መስፈርቶች ያሟሉና የደምበኞቻችን ድርጅትሁኔታና ከባቢያዊ ተፅዕኖዎችን ያገናዘበ ኦረንቴሽንና ስልጠና በመስጠት ፈተናውን በሚገባ ያለፉ ብቻ ይሆናል፡፡

የድርጅታችን እሴቶች

      • የላቀ ክብር ለደምበኞች
      • የላቀ ክብር ለጥበቃ ሰራተኞቻችን
      • ለስራችን ምንጊዜም ታማኝ መሆን (ከሁሉም አይነት ህገ-ወጥ ንክኪ ራስን መጠበቅ፣ የደምበኞችን እምነት መጎናፀፍ እና መልካም ስነ-ምግባር መያዝ)
      • የሀገሪቱን ህግማክበርና በህግ የበላይነት ማመን (ወንጀል መጥላት፣ወንጀለኛን አሳልፎ መስጠት)
      • አርኣያ መሆን (ንፁህ፣ ንቁ፣ ብርቱ ሆኖ በጥሩ ቁመና በጊዜ ስራ ላይ መገኘት)

የድርጅታችን የስራ አመራር አባላት አጭር የስራ ልምድ

ስራን የሚመራ ሲባል የሚመራው ድርጅት ወይም ተቋም ቁልፍ የሆነው ክፍል ነው ብለን እናምናለን፡፡

በእውቀትና በብቃት የሌሎችንም ሀሳብ አቅም ተሞክሮ እየተጠቀመ በየቀኑ በየግዜው በብዛት ወደ ድርጅቱ ተቀጥረው የሚገቡ የተሻለ ሊያገኙ ወይም ሳይመች የሚለቁ ተረጋግተው ተመችቷቸው የሚያገለግሉ የሚያረፍድ የሚቀር መጥፎ አመል ያለው ወዘተ ሁሉንም እንደ አመሉ በመቆጣጠር መደረግ ያለበትን በአሰራር በወቅቱ በማድረግ በትክክል አቅጣጫ መምራት ለዚህ ለ10 አመታት በተግባር የተፈተኑ በ4 ማዕዘናት በሁሉም ክልል በመግባባት በማሳመን ረጅም የስኬት አመታት ያሳለፉ አመራር አሉን፡፡

በጥበቃ አገልግሎት የብቃት ማረጋገጫ ከደንበኞች

      • ከሰራተኛ ማህበራዊ የመልካም ስራ አፈፃፀም በርካታ ሰርተፊኬቶች
      • በርካታ የምስጋና ሰርተፊኬቶች
      • በርካታ የበጎ አድራጎት ተሳትፎ ማረጋገጫ ሰርተፊኬቶች
      • በቤተ መንግስት የገቢዎች ሚኒስቴር ያዘጋጀው የከፍተኛ ግብር ከፋይ ፕሮግራም የክብር ተጋባዥ
      • የገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋይ የእውቅና ፕሮግራም ዋንጫና ሰርተፊኬት ተሸላሚ፤በሃገር ደረጃ

በጥበቃ አገልግሎት ከደንበኞች የጥሩ አገልግሎት ማረጋገጫ

1. በመልካም የሂሳብ እንቅስቃሴ እና ጤነኛ አሰራር ከ/ኢ/ን/ባንክ ሜክሲኮ ቅ.የምስጋና ደብዳቤ

2. ከሰራተኛ ማህበራዊ ህጋዊ አሰራር ሳይሸራረፍ በመተግበራቸው በየአመቱ ድንገተኛ ቁጥጥር በቢሮ በማድረግ የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃ በተደጋጋሚ አግኝተዋል፡፡

3. በየአመቱ ህግዊ አሰራሮች በመከተል ከሰራተኞቻችን ለመንግስት ገቢ የሚሆነውን በወቅቱ ገቢ በማድረግ ድርጅታችን በየአመቱ በጥሩ የስራ አፈፃፀም በወቅቱ የንግድ የስራ ፈቃዶች እንዲታደሱ ትልቁን ድርሻ ተወጥተዋል፡፡

4. ሰራተኞቻችንን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ግዜ ያገለገሉ ሰራተኞች በተገቢ በስርአት ተደራጅተው በመቀመጣችው ከደንበኞች የአባላት ሰነድ ድንገት ስንጠየቅ በማቅረብ አባላትም ሌላ ስራ ለመያዝ መልቀቂያ ጡረታ ለማስከበር የአገልግሎት እና ጡረታ መቆረጡ ማረጋገጫ ሰነድ ወዘተ ሲፈለግ እስከ ዛሬዋ ቀን ለአመታት በስርአት በተያዘው ሰነድ ተገቢ ምላሽ( አገልግሎት) በመስጠት ነባር ሰራተኞች እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

5. ከመንግስት መስሪያ ቤቶችና ከግል ባለሀብቶች በመልካም የስራ አፈፃፀም በመላው የሀገራችን ክልል ስናገለግል በርካታ የምስጋና የድጋፍ ማስረጃ ሰርተፊኬቶች ያገኘን ሲሆን በመንግስት የገቢዎች ሚኒስቴር ብዙዎች ለማግኘት የማይታደሉት ድርጅታችን ቀን ከሌት ሳንሰለች አንድ ሆነን ተቀናጅተን በመስራታችን የዋንጫና ሰርተፊኬት ተሸላሚ ማድረግ ችለናል፡፡

በጥበቃ አገልግሎት የስራ ልምድ

      • በ2012 ዓ.ም በነባሩ ድርጅታችን ስልጠና በመስጠት ሰራተኞች አ/አ ኦሮሚያ ክልል በማደራጀት ለማሰማራት ከደንበኞች በቅርበት በመገናኘት ስራ በማስተካከል በመምራት ለድርጅተሰችን እንደ ድልድይ በመሆን ወሳኝ ስራዎች ሰርተዋል፡፡
      • በድርጅታችን የተለያዩ ሳይቶች ድንገተኛ ቁጥጥር በቀንም በምሽትም በማድረግ ጠንካራውን ያበረታታሉ ደካማ እንዳይደገም በህጉ መጠን እያስተማሩ ደንበኛ በድርጅታችን አመኔታ እንዲኖረው ሰርተዋል፡፡
      • በ2013 ዓ.ም በአዳማ ኢንዱስተሪ መንደር ከፋብሪካው ሃላፊዎች ለጥበቃ ሰራተኞቻቸው ስልጠና እንድንሰጥ ተጠይቀን 1 ወር ከ300 በላይ ጥበቃዎችን ስልጠና ግሩፕ በሃላፊነት በመምራት በቲዎሪ እና በተግባር ስልጠና ከአ/አ ወር ሙሉ በመመላለስ ለፋብሪካው የሚመጥን ጠንካራ ስልጠና በመስጠት ያስመረቁ ሲሆን በዚህ ተግባር ሌሎች ኢንዱስተሪ መንደር እንድናሰለጥን ሰፊ የስራ እድል ለድርጅታችን መፍጠር ችለዋል፡፡

የጥበቃ ሠራተኞች ምልመላና መረጣ መመዘኛ የፌደራል ፖሊስ መመሪያ መሰረት

      • ከሚኖርበት አካባቢ የቀበሌ ድጋፍና ህጋዊ ቀበሌ መታወቂ የያዘ
      • ቀደም ሲል የፖሊስ ፣ የመከላከያ ሠራዊትና የሌላ የመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጣሪ የነበሩ ከሆነ ከነበሩበት መስሪያ ቤት የተሠጠ ህጋዊ መልቀቂያ ያላቸው
      • የአሻራ ምርመራ በማድረግ ከወንጀል ነፃ ለመሆኑ ህጋዊ ማስረጃ የሚያቀርብ
      • ህጋዊ ተያዥ ማቅረብ የሚችል
      • ስራውን ለመስራት ጥሩ ቁመና ያለውና፣ስለ ጤንነቱ ከሆስፒታል ህጋዊ ማስረጃ የሚያቀርብ
      • በሀገሪቱ ህጎች ፣ አዋጅ ፣ በድርጅቱ ደንብ እና መመሪያ መሠረትለመስራት ፈቃደኛ የሆነ
      • የትምህርት ደረጃ 7ኛ ክፍል እና ከዚያ በላይ
      • ራስን የመከላከል ፣ የመሳሪያ አያያዝና አጠቃቀም ችሎታና ልምድ ያላቸው ቢሆኑ ይመረጣል
      • በክብር የተሰናበቱ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት ቅድሚያ ይሠጣቸዋል፡፡
      • እድሜ ከ22 እስከ 55 ዓመት
      • በድርጅቱ የሚሠጥ ስልጠና
      • የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ፡- ተግባረቸውን ለመወጣት ያለቸውን መብትና ግዴታ እንዲያውቁ ለማድረግ
      • የሥነ-ምግባርና የሥራ መመሪያዎች፡- በድርጅቱ ውስጥ ሰራተኞች ያላቸውን መብት ግዴታ፣ በስራው እንቅስቃሴ ሊደረግ የሚገባንና የተከለከለውን ተግባር፣ የድርጀትችን ፖሊሲ፣ የአገልግሎትና የተግባር ወሰን (ማንዴት) እንዲያውቁ
      • ወንጀል መከላከልና ኮሚኒቲ ፖሊሲንግ፡- ወንጀሎችን ተገንዝበው ወንጀል የመከላከል ፍላጎታቸውን እና አመለካከታቸውን በማዳበር ከህብረተሰቡና ከፍትህ አካላት ጎን እንዲሰለፉ ለማድረግ፡፡
      • የጡረታና የግብር አዋጆች፡- የጡረታ መዋጮ ለስራ ዋስትና ያለውን ጠቀሜታ ለማስረዳትና ግብር የመክፈል ግዴታቸውንና ግብር ለህብረተሰቡ የሚሠጠውን ጥቅም እንዲገነዘቡ ለማድረግ፡፡ ደመወዝ እንዴት እንደሚሰራ የትርፍ ሰአት አከፋፈል መቼ ይከፈላል፡፡
      • የድርጅቱ የሥራና የሥነ-ምግባር መመሪያ እንዲያውቁ ማድረግ ፣ በድርጅቱና በሠራተኛው መካከል ሊኖር የሚገባ ግንኙነት፣ በሠራተኞቻችንና በደምበኞቻችን ያለ ግንኙነት ፣ የሰራተኛ መብትና ግዴታ ፣ በሠራተኛው የዕርስ በዕርስ ግንኙነት ፣ የስራ ዝምድና ፣ መልካም ሥነ ምግባር ፣ ጨዋነትና ሊተገብሩት የሚገባ የሥራ ትዕዛዞች ግንዛቤ እንዲይዙ ማድረግ፡፡
      • የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ማቋቋሚያ አዋጅ፣ የመንግስት የፀጥታና የፍትህ አካላት ስልጣንና ሀላፊነት እንዲገነዘቡ እና ለመንግስት የፀጥታ ሀይሎች የአጋርነትና የተባባሪነት ሚና እንዲጫወቱ የሚያስችል ግንዛቤ ለመፍጠር፡፡
      • ህገ-መንግስት፡- የህገ መንግስቱን መሠረታዊ አላማዎች እንዲገነዘቡ ለማድረግ
      • የጥበቃ ሙያ ትምህርቶች
      • የጥበቃ ሰራተኞቻችን የተረከቡትን ማንኛውንም ነገር ለመጠበቅ መጀመሪያ እነሱ ታማኝ መሆን አለባቸው፡፡አብዛኛው ስርቆት ጥበቃው የተሳተፈበት መሆኑ
      • የአፈታተሽ ቴክኒክና አስፈላጊነት
      • የአጠባበቅ የጥንቃቄና ደህንነት ደምቦችና የስጋት አደጋዎች መለየት
      • የደምበኞች አገልግሎት አሠጣጥና አያያዝ
      • የደምበኞች ተገልጋዮችን በአግባቡ ማስተናገድ
      • የመሳሪያ አያያዝና አጠቃቀም
      • በጥበቃ ቦታ ላይ ከውጭ አካላት ትንኮሳና አቅም መፈታተን
      • በጥበቃ ቦታ አብሮ ከሚሰራ ተደራጅቶ ወይም በግል የስርቆት ፍላጎት
      • በጥበቃ ቦታ በቀንም ሆነ በለሊት የጥበቃ መዘናጋት በተለያየ ዘዴ በማጥናት ስርቆት ይፈፀማል፡፡
      • የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና ትምህርት
      • በስራ ላይ የሚያጋጥሙ ድንገተኛ አደጋዎች አፈታት፣ አወጋገድና ከመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ጋር ሊኖር የሚገባ ግንኙነት
      • በየደረጃው ያሉ ሀላፊዎች የአመራር ተግባርና ሀላፊነት
      • የሪፖርት አፃፃፍና የግንኙነት ስርዓት

የድርጅታችን የጥበቃ አቅምና የቁጥጥር ሥርዓት ብቃት

ሀ.ተቋማዊ አቅም፡-

      • በድርጅቱ የሚገኙት አመራር አባላት በሰራዊቱ ውስጥ ለበርካታ አመታት በከፍተኛ የአመራር ሀላፊነትና በአሠላጣኝነት የሰሩ በመሆናቸው የጥበቃና የደህንነት አስፈላጊነት የደምበኞቻችንን ፍላጎት መሰረት ያደረገ አስተማማኝ የጥበቃ አገልግሎት የማደራጀትና ስራውን ተቆጣጥሮ የመምራት እውቀትና የዳበረ ልምድ አላቸው፡፡ በታማኝነት ለማገልገል የሚያስችል ስብእናና ቁርጠኝነትን የተላበሱና የፀና እምነት ያላቸው ናቸው፡፡
      • ካለን የስራ ልምድ ፣ መሰረታዊ የጥበቃ እውቀት፣ካገኘነው የጥበቃ ስራ ልምድ፣ደንበኞች ከሚሰጡን አስተያየቶች የሚገኙ ግብዓቶችን ተጠቅመን ደረጃቸውን የጠበቁ የስልጠና መርጃ እቃዎችና ማስተማሪያ ማኑዋሎች አዘጋጅተን ለጥበቃ አባሎቻችን አስፈላጊና ሙያዊ ብቃት የሚጨምሩ ሥልጠናዎችን እንሰጣለን፡፡
      • ድርጅታችን ለጥበቃ ተግባር የሚያሰማራቸው አባላት በጥበቃ ሞያ የስራ ልምድ ያላቸው ፣ ቢያንስ 7ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ፣ ከወንጀል ነፃ ስለመሆናቸው ህጋዊ ማስረጃ ያላቸው ፣ በቂ ዋስ /ተያዥ/ የሚያቀርቡና በደርጅታችን የሚሠጠውን የጥበቃ ተግባርና ሀላፊነት ትምህርት ፈተና ያለፉ ለደንበኞች ይመደባሉ፡፡
      • የምንረከባቸው የጥበቃ ቦታዎች በቀጠና የተከፋፈሉ ሲሆን ወደ ቀጠናዎች እየተንቀሳቀሱ የሚቆጣጠሩና ስራዎች በሚገባ መፈፀማቸውን የሚያረጋግጡ የቀጠና ኃላፊዎች እናሠማራለን፡፡
      • በእያንዳንዱ የጥበቃ ቦታ ላይ ሆነው የጥበቃ አባላት የሚያስተባብሩና ጥበቃውን በቅርብ የሚመሩ እንዲሁም የደምበኞቻችንን ፍላጎትና ትዕዛዝ የሚተገብሩ የሽፍት ሀላፊዎች ይመደባሉ፡፡
      • ለማንኛውም ድንገተኛ ሁኔታ ፈጣን ምላሽና እርዳታ የሚሠጥ ተረኛ ሱፐርቫይዘሮችና ተወርዋሪ ጥበቃ በማእከል በማዘጋጀት በማንኛውም ሠዓት በእቅድና በድንገት ተቆጣጣሪዎች ለፍተሸ ይንቀሳቀሳሉ፡፡
      • ከላይ ከጠቀስነው የቁጥጥር ሥርዓት በተጨማሪ ከአካባቢ ፖሊስ ኃይል፣ ከወረዳ መስተዳድር ፍትህና ፀጥታ ቢሮ እንዲሁም ከፌደራል ፖሊስ ጋር ጠንካራ ግንኙነት በማድረግ በእያንዳንዱ የጥበቃ ቦታ ላይ የሚገኙ አባላት ድንገተኛ ሁኔታ ሲፈጠር የሚያሳውቁበት ጠቃሚ ስልክ ቁጥሮች በዕለት የሁኔታ መዝገብ ውስጥ ተፅፎ ይሰጣቸዋል፡፡
      • እያንዳንዱ የጥበቃ ቦታ ውል ከተገባ በኋላ ጥበቃ ከሚደረግለት ንብረት፣ከባቢያዊ ሁኔታ፣ከደንበኞች ፍላጎት ጋር የሚስማማ የጥበቃ አፈጻፀም መመሪያ፣ቋሚ ትእዛዝ፣ የአሰራር ደንብ በዝርዝር በማውጣትና ከደንበኞች ጋር በመግባባት ስራን ለመተግበርና ለመፈፀም እንድንችል የምንጠቀምበት ሰነድ ይሆናል፡፡
      • በዚህ መሰረትም የጥበቃ አባላት እንዲያውቁት፣ በጥበቃ ቦታቸው ላይ በፁሁፍ እንዲቀመጥና ይህን መመሪያ የመፈፀም ግዴታ እንዳለባቸውም የጥበቃ አባላት በፊርማቸው እንዲያረጋግጡ ይደረጋል፡፡

 


Products and Services(4 Images)

Shared Banner Directory p8