Ethiostar Translation and Localization PLC


Mobile +251 944 062 513
Mobile 2 +251 944 094 314
LocationHouse No. 573, Opp. to Sandford Int’l School,, Addis Ababa, Ethiopia
Primary CategoryTranslation
Ethiostar Translation and Localization PLC

Who we are
Are you looking for a quality translation into any Ethiopian language, particularly into Amharic, Gurage, Hadiya, Oromiffa, Somali, Tigrinya, and Wolayta?

If yes, you are on the right track and we would like to welcome you on board.

      • We are a group of qualified translators, localization experts, and lexicographers with over two decades of working experience.
      • We have participated in localization projects for Microsoft, Google, LG, Samsung, and many more products and services.
      • We are one of the leading service providers and exporters of a wide gamut of translations from English, French, German, Italian, Portuguese, Russian, Spanish, and Arabic languages into Ethiopian Languages and vice versa.
      • We have always stood apart from our competitors due to our capacity to integrate technology (i.e. CAT Tools) into the translation process.

WELCOME
Ethiostar is a full-service Translation Agency which is registered at the Ministry of Trade and Industry of the Federal Democratic Republic of Ethiopia with the Business Number AA/AR/G7/1/001863/2012 in Addis Ababa, Ethiopia, which specializes in language translations for different businesses.

Our team consists of educated and experienced translators with a solid professional translation background and skills.
“ We repeatedly check our work to make sure you’re getting the quality you deserve - and more"

Our Mission
To provide high-quality translation services by native translators on a timely basis and at reasonable rates.

Our Vision
Our vision is to become the leading translation and localization company in the whole of East Africa; by providing language services in the major languages of the region

Our staff consists of:
Terminologists, Translators, Editors, Desktop publishing specialists, Software engineers, Interpreters, and Localization experts

ETHIOSTAR TRANSLATORS, EDITORS, AND REVIEWERS
In addition to being a native speaker of the target language and a certified language translation professional, ETHIOSTAR translators, editors, and reviewers have the following:

      • A university degree in language translation, linguistics, or a technology-related field. Many have bachelor's or master’s degrees, as well as scientific and/or technical backgrounds.
      • Background knowledge in the client’s Industry.
      • Several years of experience in the translation industry (seven years on average), including experience translating technology-related terminology and working with computer software.

Some of the translation works we do:

      • Technical Translations
      • IT Translations
      • Medical Translations
      • Legal Translations
      • Marketing Translations
      • Entrepreneurship, Business, Banking & Financial, Business Administration & Management, Marketing translations
      • Interpretation
      • Simultaneous translation
      • Sign language
      • Lexicography
      • Terminology & Etymology

What process does Ethiostar Use to translate or localize each project?

  1. Assign a project manager (PM)
  2. PM selects and assigns available translators and editors
  3. Translators and editors complete the assigned tasks
  4. The project manager returns the translated/edited files

WHY DO YOU NEED TO HIRE US
We are dedicated to high-quality translation. No students, no rookies, and no outsiders - we employ only professional and experienced translators with extensive knowledge of relevant businesses and terminology. Moreover, our bank of translation memories and real-world term glossaries makes it possible to maximize terminology consistency and translation adequacy.
We are also for the following two particular reasons:

      • We always meet deadlines for all orders from our clients.
      • Our rates are the most affordable among translation agencies worldwide.

Translation is a mental activity in which the meaning of a given linguistic discourse is rendered from one language to another. It is the act of transferring the linguistic entities from one language into their equivalents into another language. Translation is an act through which the content of a text is transferred from the source language into the target language (Foster, 1958).
Localization (also referred to as “l10n”) is the process of adapting a product or content to a specific locale or market. Translation is only one of several elements of the localization process. In addition to translation, the localization process may also include: Adapting graphics to target markets.
“Our professional and competent editors thoroughly check every translation work to achieve the highest quality possible"

ጥቂት ስለ እኛ

ወደ ኢትዮጵያ ዋና፣ ዋና ቋንቋዎች በተለይ አማርኛ፣ ጉራጊኛ፣ ሃዲያኛ፣ ኦሮሚፋ፣ ሶማሊኛ፣ ትግሪኛ እና ወላይትኛ ጥራት ያለው ትርጒም አገልግሎት ለማግኘት ይፈልጋሉ?

መልስዎ አዎ ከሆነ፣ ትክክለኛው ቦታ ላይ ነው ያሉት፤ እኛም አብረውን ሊሠሩ ስለ መጡ በደስታ እንቀበልዎታለን።

      • በሞያው ከሃያ ዓመታት በላይ ሥራ ልምድና በቂ ሥልጠና የወሰድን ተርጓሚዎች፣ ምርትን ከባቢያዊ የማድረግ ሥራ ባለሞያዎች እና የመዝገበ ቃላት አዘጋጆች ነን።
      • እንደ Microsoft: Google: LG: Samsung እና ሌሎች ታዋቂ ኩባንያዎች የሚያመርቷቸውን ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ ቋንቋዎች ከባቢያዊ በማድረግ ሥራ ላይ ከጅምሩ ጀምረን አብረናቸው ሠርተናል፤ አሁንም እየሠራን ነው።
      • ከእንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ጀርመንኛ፣ ጣልያንኛ፣ ፖርቹጋልኛ፣ ሩሲያኛ፣ ስፓኒሽኛ እና ዓረቢኛ ቋንቋዎች ወደ ኢትዮጵያ ቋንቋዎች መመለስ እና ከኢትዮጵያ ቋንቋዎችም ወደ አውሮፓ ቋንቋዎች መመለስ ሥራ ላይ መሪ ከሚባሉት አገልግሎት አቅራቢዎች መካከል የምንሰለፍ ነን።
      • ሁልጊዜ በትርጒም ሥራችን ላይ ዘመኑ ያፈራውን ቴክኖሎጂ (ለአብነት እንደ CAT መሣሪያዎች ማለትም በኮምፒውተር የታገዘ ትርጒም) ስለ የምንጠቀም እንኳን በደኅና መጡ ኢትዮስታር በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ የንግድ ሚኒስቴር በንግድ ፈቃድ ቊጥር AA/AR/G7/1/001863/2012 በአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በሕጋዊ መንገድ የተመዘገበ ለተለያዩ የንግድ ሥራ ዓይነቶች የቋንቋ ትርጒም አገልግሎት በመስጠት ላይ ያተኮረ የትርጒም አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ነው። በድርጅታችን ውስጥ ያሉ ሠራተኞች ተጨባጭ የሆነ የትርጒም ሥራ ተሞክሮና ትምህርት እንዲሁም አስፈላጊው ክኅሎቶች ያላቸው ናቸው።

“ማግኘት ያለብዎትን ጥራቱን የጠበቀ ትርጒም አገልግሎት እንዳገኙ ለማረጋገጥ የምንተረጒምልዎትን ሰነድ ደጋግመን እናረጋግጣለን።"

የእኛ ተልዕኮ
አፍ መፍቻቸው በሆኑ ተርጓሚዎች ወደ የሚፈለገው ቋንቋ ከፍተኛ ጥራት ያለው የትርጒም አገልግሎትን በሰዓቱና በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ።

የእኛ ራእይ
የእኛ ራእይ በመላው ምሥራቅ አፍሪካ በክልሉ ውስጥ ባሉት ዋንኛ ቋንቋዎች የትርጒም አገልግሎቶችን በማቅረብ ግንባር ቀደም የትርጒምና ምርትን ከባቢያዊ የማድረግ ሥራ አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያ ሆኖ መገኘት ነው።

የሚከተሉት ሠራተኞች አሉን፦
የቃላት ልሂቃን፥ ተርጓሚዎች፥ አርታዒያን፥ የዴስክቶፕ ኅትመት ባለሞያዎች፥ ሶፍትዌር መሐንዲሶች፥ ትርጁማኖች፥ ምርትን ከባቢያዊ የማድረግ ሥራ ባለሞያዎች ኢትዮስታር ተርጓሚዎች፣ አርታዒያን፣ እና ገምጋሚዎችትርጒም አገልግሎት በሚሰጥበት ቋንቋ አፋቸውን የፈቱና የትርጒም አገልግሎት የሞያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው ከመሆናቸው ባሻገር፣ የኢትዮስታር ተርጓሚዎች፣ አርታዒያን እና ገምጋሚዎች የሚከተሉት ተጨማሪ እሴቶች አሏቸው፦

      • በቋንቋ ትርጒም ሥራ፣ የቋንቋ ጥናት ወይም ከቴክኖሎጂ ጋር ተዛማጅነት ባለው መስክ የዩኒቨርስቲ ዲግሪ።
      • አብዛኛዎቹ የመጀመሪያ ወይም ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው ከመሆናቸው በተጨማሪ የሳይንስ እና/ወይም የቴክኒክ ድህረ ታሪክ ያላቸው ናቸው።
      • በደንበኛው ኢንዱስትሪ መስክ የራሳቸው ልምድና ተሞክሮ።
      • ቴክኖሎጂ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ቃላት መተርጐም እና በኮምፒውተር ሶፍትዌር መሥራትን ጨምሮ በትርጒም ሥራ ኢንዱስትሪ ውስጥ የበርካታ ዓመታት የሥራ ልምድ (በአማካይ ሰባት ዓመት)።

እኛ ከምንተረጒማቸው ሥራዎች መካከል

      • ቴክኒካዊ ትርጒም አገልግሎት፥
      • አይቲ ትርጒም አገልግሎት፥
      • ሕክምና ነክ ጉዳዮች ትርጒም አገልግሎት፥
      • ሕግ ነክ ጉዳዮች ትርጒም አገልግሎት፥
      • የገበያ ፈጠራ ትርጒም አገልግሎት ፥
      • ሥራ ፈጠራ፣ ንግድ ሥራ፣ ባንክ እና ፋይናንስ፣ ንግድ ሥራ አስተዳደር፣ የገበያ ፈጠራ ነክ ትርጒም አገልግሎቶች
      • ትርጁማን ትርጒም አገልግሎት
      • የኮንፈረስ ትርጒም አገልግሎት፥
      • የምልክት ቋንቋ
      • የመዝገበ ቃላት ዝግጅት
      • የቃላትና ሥርወ ቃል ጥናት

በእያንዳንዱ ፕሮጄክት ላይ ኢትዮስታር ለመተርጐም ሆነ ምርትን ከባቢያዊ ለማድረግ ምን ዓይነት ሂደትን ይከተላል?

  1. የፕሮጄክት ሥራ አስኪያጅ ይመደባል
  2. ፕሮጄክት ሥራ አስኪያጅ መሥራት ከሚችሉ ተርጓሚዎች እና አርታዒያን መካከል መርጦ ሥራውን ይሰጣቸዋል
  3. ተርጓሚዎች እና አርታዒያን በቅደም ተከተላቸው ሥራቸውን ሠርተው ያጠናቅቃሉ
  4. ፕሮጄክት ሥራ አስኪያጅ የተተረጐመውን/አርትዕ የተደረገውን ፋይል ለደንበኛው ተመላሽ ያደርጋል።

ከእኛ ጋር ቢሠሩ ምን ጠቀማሉ
ከምንም በላይ ከፍተኛ ጥራት ያለውን ትርጒም ሥራ ሠርቶ ለማቅረብ ቁርጠኛ ፍላጐት አለን። ምንም ዓይነት ተማሪ ተርጓሚዎች፣ ድንገቴ ተርጓሚዎች እና ሥራው የማይመለከታቸው ግን ቋንቋ በማወቃቸው ብቻ እንተረጒማለን የሚሉ ሰዎችን በሥራችን ውስጥ አንጠቀምም - በሚተርጒሙት ጉዳይ ዙሪያ በቂ ዕውቀትና የሥራ ልምድ ያላቸውን በቂ ትምህርትና ዝግጅት ያላቸውን ፕሮፌሽናል ተርጓሚዎችን ብቻ ቀጥረን እናሠራለን። ከዚህ በተጨማሪ የራሳችን የቃላት ፍቺ ባንካችን እና ከእውነታው ዓለም ጋር የተጣጣሙ ሙዳየ ቃላት መዝገባችን የምንጠቀምባቸውን ቃላት ወጥነት ያላቸው እና የምንሰጠው የትርጒም አገልግሎትም የላቀ እንዲሆን ማድረግ ያስችለናል።
በሚከተሉት ሁለት ዋንኛ ምክንያቶች በተለይ እኛ ተመራጭ ነን፦

      • ከክቡራን ደንበኞቻችን ለሚሰጠን የሥራ ትዕዛዝ ያለ ምንም ወለም ዘለም በሰዓቱ ሠርተን እናስረክባለን።
      • በዓለም ዙሪያ ተመሳሳይ አገልግሎት ከሚሰጡ የትርጒም አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች አኳያ ሲታይ የእኛ ዋጋ ብዙም ኪስን የሚጐዳ አይደለም።

ትርጒም ሥራ
ትርጒም ሥራ በአንድ ቋንቋ የተሰጠ አንደምታን ለዛና ስሜቱን ሳያጣ ወደ ሌላ ቋንቋ እንዳለ የማስተላለፍ አእምሮን የሚጠቀም ሥራ ነው። በአንድ ቋንቋ ያሉትን አለባውያን በሌላ ቋንቋ ወደ ያሉት አቻ ፍቺዎች የማስተላለፍ ተግባር ነው። ትርጒም ሥራ የአንድ ጽሑፍ ይዘት ከምንጭ ቋንቋ ወደ ዒላማ ቋንቋ የሚተላለፍበት ሥራ ነው (Foster, 1958).

ምርትን ከባቢያዊ ማድረግ
ምርትን ከባቢያዊ ማድረግ (በእንግሊዝኛ ቋንቋ በተጨማሪ“l10n” በመባልም ይታወቃል) አንድን ምርት ወይም ይዘት ለአንድ የተወሰነ አካባቢ ወይም ገበያ በሚስማማ መልኩ እንዲቀርብ የማድረግ ሂደት ነው። ትርጒም አገልግሎት ከምርትን ከባቢያዊ ማድረግ በርካታ አባለ ነገሮች መካከልአንዱን ገጽታ ብቻ የሚወክል የሂደቱ ክፍል ነው።

ከትርጒም አገልግሎት በተጨማሪ፣ ምርትን ከባቢያዊ የማድረግ ሥራው ሂደት የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፦ ሥዕሎችን፣ ምስሎችን ወዘተ ዒላማ ከተደረገው ገበያ ጋር እንዲስማሙ ማድረግ።

“ፕሮፌሽናልና በሞያው ብቃታቸው የተረጋገጠ የእኛ አርታዒያን ማግኘት የሚቻለውን ከፍተኛ ጥራት ያለው ትርጒም ሥራን ለማስገኘት እያንዳንዱን የትርጒም ሥራ በጥንቃቄ ደጋግመው ይፈትሻሉ"

 

Contact Us
Address:- House No. 573, Opp. to Sandford Int’l School,
Mobile No:- +251 944 062 513
                    +251 944 094 314
Email:- info@ethiostarlocalization.com

 


Shared Banner Directory p8