Phone | 0116-72-2008 |
Phone 2 | 0228-12-7490 |
Fax | 0116-72-2240 |
Mobile | 0974-18-1910 |
Mobile 2 | 0900-80-9098 |
Location | Addis Ababa/Finfine(Head Office I) around Bole Medhanealem Church, Oromia Bldg 2nd floor , Adama/Nazareth (Head Office II) around Mebrat Hayl, Minch Gebeya Bldg 2nd floor, Addis Ababa , Adama, Ethiopia |
Primary Category | Security/Guard Services |
“Looyaal Sakuriitii W.A”፤ “ሎያል ሴኩሪቲ አ.ማ”፤ “Loyal Security S.C”፤ (የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጄንሲ/Private Employment Agency፤ ከዚህ በኋላ “ሎያል ሴኩሪቲ” ተብሎ የሚጠራው)፤ በተለይም “በሴኩሪቲ ኢንደስትሪ መስክ/ሴክተር”፤ በደንበኛ ሙሉ አውትሶርስ (Full Outsource) ሥራ ላይ፤ በግል የሥራ አገልግሎት ቅጥር ውል፡- አገር ውስጥ፤ ሲቪል የግል የሴኩሪቲ ሥራ አገልግሎት ሰጪ ኤጄንሲ (Local Civil Private Security Provision Employment Agency) በመሆን፤ ሥራ አጥነትንና ድህነትን በመቀነስና የሥራ ዕድልን ለወጣቶች ለመፍጠር፤ ማኅበራዊ ግዳታን በአግባቡ መወጣት፤ በዚሁ የሥራ ዘርፍ/መስክ፤ ጉዳዩ በሚመለከተው ሴኩሪቲ ኢንደስትሪ ባለሥልጣን (Security Industry Authority) ሥር፤ ከፖሊስ በተጨማሪ የመንግሥት lዩ አጋዥ ኃይል ሆኖ አስቀድሞ ወንጀልን በመከላከልና መንግሥትንም በመደገፍ፤ ብሎም እድገትንና ልማትን በማፋጠን፤ ደንበኞችን በአስተማማኝ ሴኩሪቲ (ጥበቃ) ሥራ በማገልገል፤ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 10፤ አንቀጽ 11(3)፤ እንዱሁም በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 2 (ትርጓሜ፣ ንዑሣን አንቀጽ 13፤ 13/ለ፤ 16) እና፤ አሁንም በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 171 እና አንቀጽ 174 ድንጋጌዎች፤ ወዘተ. መነሻነት፤ በጊዜው አሁን በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር/ሚኒስትር የአፈፃፀም መመሪያ መሠረት፤ ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ሥራ፤ ሙያተኛ ሠራተኞችን በኃላፊነት በሙያው እየቀጠረና እያሠለጠነ፤ በአዲስ አበባ ከተማና በመላው የአገሪቷ ከተሞች፣ ክልሎችና ዞኖች ሁለ፤ ለተለያዩ ተቋሞች/ድርጅቶች “ሲቪል የግል የሴኩሪቲ ሥራ አገልግሎት በዋናነት”፤ እንዱሁም በተጓዳኝ የጽዳት፣ የሰው ኃይል አቅርቦት፣ የቢሮ ሥራ፣ የሾፌርነት፣ የጉልበት ሥራ፣ የአትክልት እንክብካቤና፣ ሌላ ተዛማጅ የሥራ ዘርፎች ጨምሮ አገልግሎት የሚሰጥ፤ በኢትዮጵያ ንግድ ህግ መሠረት፤ በ19 ባለ አክሲዮኖች አባላት እና በብር 17,950,000.00 (አሥራ ሰባት ሚሉዮን ዘጠኝ መቶ ሃምሣ ሺህ ብር) መነሻ ካፒታል ፤ ይኸውም፡- የአንድ አክሲዮን ነጠላ ዋጋ ብር 10,000.#(አሥር ሺህ ብር) ሆኖ፤ በድምሩ በ1,795 አክሲዮኖች የተቋቋመ፤ ህጋዊ ሰውነት (ዕውቅና) ያለው የንግድ ማኅበር ነው፤ (ማለትም፡- የሴኩሪቲ ኢንደስትሪ ነው፤ የሴኩሪቲና የጃንቶሪያል አክሲዮን ማኅበር ነው)፡፡
ዓላማ፡-
ሎያል ሴኩሪቲ አክሲዮን ማኅበር ዓላማው(Purpose)፡- በእሴቶች በመመራት፤ ግልጽ የሆነ የሥራ ግንኙነትና ትስስር ሽቅብ ወደ ላይ፣ ቁልቁል ወደ ታች እና ወደ ጎን በቻርት የሚያሣይ፤ የባለድርሻ አካላትን ተግባርና ኃላፊነት በዝርዝር የሚያስረዳ፤ ተልዕኮን በቀላል በውጤታማነትና በስኬታማነት መወጣት የሚያስችል ፤ ለማኅበሩ የሥራ አመራር አካል (ለዳይሬክተሮች ቦርድ) ምቹና ቀላል የሆነ፤ ራዕይን እውን የሚያደርግ፤ በቀጥታ ሥራውን በግልጽነትና በተጠያቂነት በተቀናጀ የጋራ አመራር በሥራ መሪዎች (Managerial Employees) በትክክል ለመምራት የሚያግዝ የድርጅቱ ተቋማዊ አደረጃጀት/መዋቅር እውን እንዲሆን ማድረግ እና፣ “በመመሥረቻ ጽሐፍ” እና “በመተዳደሪያ ደንብ” በዋናነት የተዘረዘሩትን የማኅበሩን ዓላማዎች እና፣ በቦርደ ቃለ-ጉባኤ የዳበሩትን ተያያዥነት ያላቸውን ሌሎች ሥራዎች ሁለ ወደ ተግባር መተርጎም ነው፡፡
ሎያል ሴኩሪቲ፡- ራዕይ፤ ተሌዕኮ፤ እሴቶች፤
ራዕይ፡-
በ2022 በሴኩሪቲ ኢንደስትሪ ዘርፍ በመላ አገሪቷና በምሥራቅ አፍሪካ (በአፍሪካ ቀንድ) ግንባር ቀደም ተመራጭ፤ ብቃትና ጥራት ያለው፤ በዘመናዊ ቴክኖልጂ የሚታገዝ ሴኩሪቲ ተፈጥሮ ማየት፡፡ተልዕኮ፤ ሎያል ሴኩሪቲ ዋና መ/ቤቱ ፊንፊኔ/አዲስ አበባ ከተማ እና፣ አዳማ (ኦሮምያ) ሆኖ፤ ቅርንጫፍ መ/ቤቶችን ደግሞ በመላ ኦሮምያ ዞኖችና ከተሞች፤ እና በሌሎች ክልሎች ሁሉ፤ እንዱሁም ከኢትዮጵያ ውጪ በመክፈት፤ የአገሪቷ ህግና የመንግሥት ፍላጎት መሠረት በማድረግ፤ ጥራትና ብቃት ያላቸውን ወጣት የሴኩሪቲና ደኅንነት፣ እንዱሁም የጽዳት ሙያተኞች በማቀፍ፡- ጊዜው የሚጠይቀውን እስታንዳርድ የያዘ፤ ደንበኞቹን የሚያረካ ጥራትና ብቃት ያለው የሴኩሪቲና ደኅንነት፣ እንዱሁም የጽዳት አገልግሎት መሥጠት፤ ቀጥሮ ከሚያሠራቸው ሙያተኞች ጋር መልካም የሥራ ግንኙነት መመሥረት፤ በዘመናዊ ቴክኖልጂ በመታገዝ፤ የሴኩሪቲ ሥራን ማዘመን፤ የሴኩሪቲና ደኅንነት መቆጣጠሪያ መሣሪያዎችን ለተገልጋይ ደንበኞች ማቅረብ፤ በዘርፉ እንደ ፖሊስ፣ መንግሥትንም መደገፍ፤ የሴኩሪቲውን አካባቢ ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግ ይቻል ዘንድ፡- ከመንግሥት አስተዳደርና ፀጥታ ኃይል ፤ ከፖሊስ ክፍል፤ ከኅብረተሰብ-አቀፍ ፖሊስ አካል (Community Policing Police Station) እና፣ ከኅብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ በኅብረት መሥራት፤ ወንጀልንና ጥፋትን አስቀድሞ በጋራና በቅንጅት መከላከል፤ የደንበኛ ገንዘብ፣ ንብረት/ሃብት፣ ቁሳቁስ፣ የሥራ መሣሪያ ሁለ እንዳይጠፋ፣ እንዳይሠረቅ፤ በውጭ ኃይልና ሰርጎ-ገብ ሆን ተብሎ የስለላ/የተንኮል ተግባር እንዳይፈፀምበት አስቀድሞ መከላከልና መጠበቅ፤
በአስፈላጊ ትጥቅም ሆነ ይህ በሌለበት ሁኔታ የደንበኞችን ሕይወትና ንብረት/ሃብት በንቃት፣ በታማኝነትና በጥንቃቄ መጠበቅ፤ ወንጀልንና ጥፋትን አስቀድሞ መከላከል፤ ወንጀል/ጥፋት ተፈጽሞ ቢገኝ በወቅቱ ፈጥኖ በቦታው/በሣይቱ ላይ በግንባር በመገኘት ወንጀል/ጥፋት ፈጻሚውን አካል በተባበረ ማስረጃ ጉዳዩ ለሚመለከተው የፍትሕ አካል ማቅረብ፤ መከታተል፤ ማኅበሩን Learning Organization ኤጀንሲ አድርጎ ማደራጀት፡፡
እሴቶች፤ እኛ ሎያል ሴኩሪቲ ውስጥ ያለነው ከፍተኛ ሙያተኛ ሠራተኞች በሙሉ በሚከተሉት እሴቶች (VALUES) እንመራለን፡-
የአድራሻችን የቦታው የአቀማመጥ ንድፍ (ስኬች/Sketch)፡-
አገልግልት የሚሰጥባቸው፡- የሥራ ሥምሪት ዘርፎች፤ ተቋማት፤ እና የአገልግልት ዓይነቶች፤
አገልግሎት የሚሰጥባቸው ተቋማት፡-
የአገልግሎት ዓይነቶች፡- ሎያል ሴኩሪቲ ከላይ ለተመለከቱት ተቋማት ሁሉ በየሥራ ሥምሪት ዘርፎቹ የሚከተሉት ሲቪል የግል የጥበቃ አገልግሎት ዓይነቶች (Types of Security Services: Civil Private Security Activites of Employment Agencies & Recruiting Organizations) ሥምሪት ይሰጣል፡፡
ይኸውም፡-
i. የሠለጠነ የሴኩሪቲ (የጥበቃ) ሥራ ሙያተኞች ሥምሪት አገልግሎት፤ Security Employment Services፤
ii. የቢሮ ሥራ ሙያተኞች እና፣ የተዛማጅ ተግባር ሠራተኞች ሥምሪት፤ በተለይ በተእያዩ ሙያዎች ከዩኒቨርሲቲ ኮሌጆች የተመረቁ ወጣቶች ሥምሪት፤ ሾፌሮች፤ ሞተረኞች፤ እንግዲ ተቀባዮች፤ ጽዳት ሠራተኞች/ተላላኪዎች፤…ወዘተ. ጭምር፤
iii. ወቅታዊ (ጊዜያዊ) የጥበቃ ተግባር/ሥራ ሥምሪት፤ ማለትም፡- ለ”VIP/ቪ.አይ.ፒ” ጥበቃና እጀባ፤ ለሠርግ፤ ለስፖርት በዓሎች፤ ለግብዣና ለመሳሰለት የሚሰጥ ጊዜያዊ የጥበቃ ተግባር ሥምሪት፤
iv. ቋሚ የግል እጀባ፣ የባለሥልጣን እጀባና ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው የምርቶች እጀባ ሥምሪት፣
v. የንብረት ግ/ቤቶች፤ የመጋዘኖችና የመ/ቤቶች ጠባቂዎች ሥምሪት፤
vi. የጽዳት ሥራ ሙያተኞች ሥምሪት፤
vii. የአትክልተኞች ሥምሪት፤
viii. የጉልበት ሠራተኞች ሥምሪት፤
ix. የግንዛቤ ማስጨበጫ፤ እንዱሁም የአጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ የሴኩሪቲ ሥልጠና አገልግሎት መስጠት፤
x. በጥበቃና ደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያ ሙያዊ የምክር አገልግሎት መሥጠት፤….. ወዘተ. ናቸው፡፡
ተቋማዊ የአቋም መዋቅር(ቻርት/Chart) (Organizational Structure)
ሎያል፡- ታማኝ አገልጋይ!!
LOYAL: The Trustworthy Security Compay!!
Loyal Security S.C. the Home of Electronics Security!!
Contact Us
Address:- Addis Ababa/Finfine(Head Office I) around Bole Medhanealem Church, Oromia Bldg 2nd floor
Adama/Nazareth (Head Office II) around Mebrat Hayl, Minch Gebeya Bldg 2nd floor
Phone: 0116-72-2008
0228-12-7490
Mobile: 0974-18-1910/0900-80-9098
Postcode:- 80919
Email:- loysecs@gmail.com , xookkee@gmail.com
Website:- www.loyalssc.com
Fax:- 0116-72-2240